“ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ
በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ”
የሚላት የመጀመሪያዋን ቀዳማዊት ሄዋን ነው
“ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ
መጽናናያ ሆኖኛል፣ ክሶኛል ፍቅርሽ”
ሲል ደግሞ ይኽቺ ዳግማዊት ሄዋን እመቤታችን ማርያም ሆና፣ በልጇ በክርስቶስ እንደካሰችን ነው የሚያሳየው።
~ ቴዲ አፍሮ
“ልቤም ተደላደለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንቺን ስለመውደዴ፣ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድን ነው?
ቢጠፋም ስሜ ነው።
በዚህች ዓለም ስኖር ሰው ነበር ረሀቤ
ምኞቴ ተሳካ ባንቺ አረፈ ልቤ…”
እያለ ነው እንግዲህ ዘፈኑ ጀምሮ……….
“ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ
በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ
ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ
መጽናናያ ሆኖኛል፣ ክሶኛል ፍቅርሽ”
የሚለው ጋ የሚደርሰው። እንዲህ ቅልጥ ባለ እና ቅልጥ በሚያደርግ የፍቅር ዘፈን ላይ፥ ይኼ ማርያምን ነው የሚገልጸው ማለት ለምን እንደሚጠቅም አላውቅም። አንዳንዱ ነገር ባይብራራ ሳይሻል አይቀርም።
* * *
ጎሳዬ ተስፋዬ

“እናትዬ የሚለውን ለማን ነው የዘፈንከው?” ሲባል
“ለእናቴ” አለ ብለው ሲያነፍሩን ነበር። (ቃለ መጠይቁን አልሰማሁትም) እንግዲህ “ሁለት እናት አለኝ…” ሁሉ የሚል ሀረግ አለው።
Published on November 27, 2017 18:03