Jump to ratings and reviews
Rate this book

አፍ

Rate this book

254 pages, Paperback

First published March 15, 2018

3 people are currently reading
74 people want to read

About the author

አዳም ረታ

13 books186 followers
አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው አጫጭር ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት።

‹ማሕሌት›፣ ‹አለንጋና ምስር›፣ ‹እቴሜቴ ሎሚ ሽታ›፣ ‹ከሰማይ የወረደ ፍርፍር›፣ ‹ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ›፣ ‹ሕማማትና በገና› የተሰኙ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሀፍትን በግሉ አሳትሟል፡፡

የአዳም የረዥም ልብወለድ ሥራ የሆኑት ‹ግራጫ ቃጭሎች› እና ‹መረቅ›ም በብዙ አንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

አዳም ረታ በአጻጻፍ ስልቱ ልዩ፣ በቋንቋ አጠቃቀሙ ማራኪ እና በሚያነሳቸው ሀሳቦች ምጡቅ ደራሲ እንደሆነ የስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎችና የሥራዎቹ አንባቢዎች ይመሰክራሉ፡

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
17 (48%)
4 stars
9 (25%)
3 stars
3 (8%)
2 stars
5 (14%)
1 star
1 (2%)
Displaying 1 - 3 of 3 reviews
Profile Image for Martha H. Kidane.
46 reviews30 followers
June 5, 2022
ከዚህ በፊት ካነበብኳቸው የአዳም ጽሑፎች ይኸኛው በመጠኑ ልዩነት የሚያሳይባቸው ነጥቦች አሉት። እስካሁንም ከውስጤ ላወጣው ያልቻልኩት እና በሚገርም ምስል ከሳችነት የተገለጸ የለውጥ ታሪክን ይዟል። ትረካው ማራኪ ነው።
This entire review has been hidden because of spoilers.
Profile Image for Jared Donis.
331 reviews58 followers
November 25, 2023
አዳም ረታ “የቅልልቦሽ ግማሽ ጨዋታ” ብሎ በሰየመው የድርሰት ቅርጽ በታቦት ማደሪያ ሰፈር የሚኖሩ የአምስት ወጣቶችን ሕይወት የሚተርክበት ሌላው ድንቅ ስራው ነው።

ይህ ድርሰት ጥልቅ የትራጀዲ ታሪክ እንደሆነ ያስተዋልኩት ሙሉውን መጽሐፍ አንብቤ ከጨርስኩ በኋላ ነው። ገና ላላነበቡት ሰዎች ስል ዝርዝሩን አልናገርም። በኢትዮጵያዊነታችን ይሁን በሌሎች ምክንያቶች በተገቢው ዕድሜ በሙላት መኖርን እና በሙላት ማፍቀርን ሳናይ ወይም ለመሞከር ፈርተን እንዲሁ ተነካክተን እንደምናልፍ፤ ገና በልጅነት ወደፊት ጸጸት እና ናፍቆት የሚጭሩብንን ገጠመኞች እንደምናስተናግድ እና አብዛኞቹ የአዋቂነት ዕድሜ ላይ የምንኖርባችው ልምዶቻችን ክሽፈት የወለዳቸው ፍልስፍናዎቻችን እንደሆኑ ተረድቼበታለሁ።

እንዲያው ከመጽሐፉ ምንም የምወስደው አስተምህሮ የለም ብዬ ባስብ እንኳ ደራሲው ድንቅ አድርጎ ስለጻፈው በልብ-ወለድ ታሪክነቱ ብቻ የማነብበው ስራ ነው። የምንኖርበት ገሃድ ምን ያህል አስደናቂ ዝርዝር እንዳለው ቆም ብለን የምናጤነው እና እውነታው በሚገለጥበት የቋንቋ ጉልበት የምንደነግጠው በአዳም ረታ ስራዎች ውስጥ ብቻ ነው። አዳምም ታዋቂ ደራሲ ሆኛለሁ የሚል ትዕቢት ሳይዘልቀው በስሙ ብቻ ማሳተምና ገንዘብ መሰብሰብ ስላለበት የማይጽፍ ደራሲ መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሮአል። በዚህ እጅግ አከብረዋለሁ። መክሊቱን ሁሌም እያሳደገ ከልቡ የሚጽፍ ሰው ነው። በዚህ ዘመን ኖሮ የእርሱን ስራዎች ማንበብ መቻልም መታደል ነው።

እንደ ድርሰቶቹ ከሆነ በእግዚአብሔር ማመኑን እርግጠኛ ባልሆንም አዳም ሆይ እግዚአብሔር ባርኮህ እጅግ ብዙ ጽፈህ አስነብበን ብዬ መርቄዋለሁ።
1 review
July 26, 2020
how can i read this book without getting it?
This entire review has been hidden because of spoilers.
Displaying 1 - 3 of 3 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.