Jump to ratings and reviews
Rate this book

ተረት ተረት የመሰረት

Rate this book

Paperback

First published January 1, 1955

31 people are currently reading
603 people want to read

About the author

ሀዲስ ዓለማየሁ

5 books279 followers
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ከዚህ ባሻገር:

የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት
ተረት ተረት የመሰረት
ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
15 (38%)
4 stars
5 (12%)
3 stars
7 (17%)
2 stars
3 (7%)
1 star
9 (23%)
Displaying 1 of 1 review
Profile Image for Theodros Atlaw.
7 reviews25 followers
March 16, 2021
የሀዲስ አለማየሁ የመጀመሪያ የታተመ መጽሐፍ የሆነው “ተረት ተረት የመሠረት” በሦስት የተለያዩ ጊዜያት ይዘቱን እየቀያየረ ታትሟል፡፡ በ1948 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲታተም አስራ አንድ ተረቶችን ይዞ ነበር፤ የ1962ኡ ሁለተኛ ህትመት የተረቶቹን ይዘት ሳይቀይር ነገር ግን አጋዥ ስዕሎች ተጨምረውበት ታተመ፤ በ1985 መጽሐፉ ለሦስተኛ ጊዜ ሲታተም፣ ስዕሎቹ ቀርተው አምስት አዳዲስ ተረቶች ታክለውበት መግቢያም ተሠርቶለት ወጥቷል፡፡ ይህ የመጨረሻው እና ተደጋግሞ የታተመው ህትመት በውስጡ አስራ ስድስት ተረቶችን የያዘ ሲሆን፣ ተረቶቹ በአብዛኛው ዋነኛ ባለታሪኮቻቸው እንሰሳት ናቸው፤ በተረቶቹ ውስጥ ሰዎች ቢገኙ እንኳን ፍዝ ሚና ኖሯቸው ነው የተመሰሉት፡፡ እንደ ሞት፣ እርጅና እና በሽታ ያሉ ረቂቅ ሀሳቦች ሥጋ ለብሰው የሚመጡበት ተረትም በመድበሉ ውስጥ ተካቷል፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኛቸው አብዛኞቹ ተረቶች ከላይ ከላይ ሲታዩ ተቀብለናቸው የምንኖራቸው ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች፣ የሰዎች እና የእንሰሳት ግንኙነቶች፣ የእንሰሳት የእርስ በርስ ግንኙነቶች፣ የእንሰሳት ባህርያት፣ የእንሰሳት ተፈጥሮ እንዴት አሁን ያለበት ደረጃ እንደደረሰ የሚገልጡ፣ ኢሶዶሬ ኦክፔሁ "ገላጭ" የሚላቸው ዐይነት የእንሰሳት ተረቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በቅሎ ለምን እንደማትወልድ፣ ጅቦች ለምን ፊትና ኋላ እንደማይሄዱ ወይም ለምን የቡዳ ምሳሌ እንደተደረጉ፣ እንሰሳት እንዴት ወደ ሳርበል እና ሥጋበልነት እንደተከፋፈሉ እና አንበሳም እንዴት "ንጉሠ አራዊት" እንደሆነ፣ እንዲሁም አይጥ እና ድመት መሐል ለምን ጠላትነት እንደተፈጠረ ይነግሩናል፡፡
ደራሲው ተረት "ተወዳጅ እንዲሆንና ደስ እያለ እንዲነበብ አፋዊ መልኩ ወይም የሞራሉ ጌጥ ደህና ሆኖ የተሰራ እንዲሆን ያስፈልጋል" እንደማለታቸው ተረቶቻቸውን በተመሠከረለት የአከያየን ክህሎታቸው አንባቢን ይዘው የሚያቆዩ አድርገው ደርሰዋቸዋል፡፡ እንደ ቃላዊው ተረት አንድ መስመር የሚከተሉ የታሪክ አወቃቀሮች፣ ያልተወሳሰቡ ታሪኮች፣ በአብዛኛው በድርጊቶቻቸው እና በንግግሮቻቸው በቀላሉ የምንተዋወቃቸው ገፀባህርያት፣ የማያደናቅፍ ቋንቋ የሀዲስ ተረቶች መለያዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ተረቶች ጽሑፋዊው የተረት ዘውግ ከቃላዊው ተረት በተዋሰው ስልት መሠረት ሁሉም ከአፋዊው አጫዋችነታቸው፣ ከጊዜ ማሳለፊያነታቸው ባሻገር ለአንባቢው (እንደየመረዳቱ) የሚሰጡት ትምህርት ወይም "ሞራል" አላቸው፡፡ ሀዲስ በተረቶቻቸው ደግነትን፣ ብልህነትን፣ ተስማምቶ መኖርን፣ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን እና የመሳሰለውን ሲሰብኩ፤ ስግብግብነትን፣ ክፋትን፣ ከንቱ ውዳሴን፣ ሞኝነትን፣ በሌላው ላይ መፍረድን እና የመሳሰለውን ያወግዛሉ፡፡
Displaying 1 of 1 review

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.